ሕፃናት ክፍል
ሕፃናት ክፍል ሲሰራ የነበረው
- ሰንበት ትምህርት ቤቱ በተቋቋመበት በ___ዓመት የሕፃናት መርሐግብር ተቋቋመ በዚህ መርሐግብር የሚማሩ በእድሜ ከ4-17ዓመት ያሉት ሕፃናት እና አዳጊዎች ናቸዉ።
- ለማስተማር እንዲያመችም በየ እድሜያቸው መሰረት ከፍሎ ምድብ በመስጠት ትምህት፣መዝሙር፣ኪነ-ጥበብ፣ እደጥበብን እና ቅዱሳን ሥዕላት መሳልን ሲያስተምህር ቆይቷል።
- የአባላት መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ለማሳደግ የተለያዩ ስልጠናዎችን፣የጉዞ መርሐግብሮች ያዘጋጃል የንሰሐ አባት እንዲኖራቸው በማድረግ ሁለገብ ሕፃናትን አፍርቷል።
- በአስኳላ ትምህርታቸው ጎበዝ እንዲሆኑ የጥናት መርሐግብር አዘጋጅቶ ያስተምራል።
- ሰንበት ትምህርት ቤት እና ወላጆች ጥብቅ የሆነ ግንኙነት እንዲኖራቸው ወላጆችን ጠርቶ ያወያያል የተለያዩ ልዩ መርሐግብሮች ላይ ተገኝተው እንዲሳተፉ የማድረግ ስራዎችን እየሰራ ቆይቷል።
አሁን እየሰራ ያለው ስራዎች
- ከዚህ በፊት እየተሰራ የነበሩትን ስራዎች እና ተሞክሮዎችን በመውሰድ በተሻለ ሁኔታ እየሰራ ይገኛል።
- የአባላትን መረጃ ከሚዲያ ክፍል ጋር በመሆን በሃርድ ኮፒ የነበረውን ወደ ዲጂታል በመቀየር የተማሪዎቹን መረጃ በአግባቡ ይዞ ለተማሪዎች የመዝሙር ምድብ እና ትምህርት የሚማሩበትን ክፍል ያሳውቃል፣ይከታተላል፣ይረዳል።
- በመዝሙር ጥናት :-ከዚህ በፊት ተማሪዎች በእድሜ ቢለዩም ነገር ግን በእድሜ ተመሳሳይ የሆኑት ነባር እና አዳዲስ አባላት አንድ ላይ ያጠኑ ነበር ይህ ደግሞ ለማስተማርም ለአገልግሎትም አስቸጋሪ ስለሆነ በአሁኑ ሰዓት በ5 ምድብ ተከፍሎ መዝሙር ያጠናሉ እነርሱም ከ4-7 ዓመት ያሉት ቂርቆስ ምድብ አገልግሎት ያልጀመሩ ከ8-12 ዓመት ያሉት ባህራን ምድብ ከ13-17ዓመት ያሉት ዱራታኦስ ምድብ በተመሳሳይ ሁኔታ አገልግሎት የጀመሩት ደግሞ ከ8-12 እስጢፋኖስ ከ13-17 እድሜ ያሉት በርናባስ ምድብ በሚባል ምድቦች ተከፍሎ መዝሙር ያጠናሉ ከአንዱ ምድብ ወደ ሌላ ምድብ የሚሻገሩበት የራሱ የሆነ ህግ እና መዋቅር አለው ።
- በትምህርት :-በቅዱስ ሲኖዶስ መሪነት በሰንበት ትምህርት ቤቱ መምርያ በወጣው ዓለም አቀፍ አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ በማድረግ ከትምህርት እና ስልጠና ክፍል ጋር በመሆን እያስተማረ ይገኛል።
- ልዩ ልዩ ትምህርቶች :- ኪነ-ጥበብ እና የቅዱሳን ሥዕላት መሳል እያስተማረ ይገኛል በተጨማሪም በዓለማዊ(በአስኳላ) ትምህርታቸው ጎበዝ/ጠንካራ እንዲሆኑ በእረፍት ጊዜያቸው ክረምት ላይ መርሐግብር አዘጋጅቶ እንዲማሩ ያደርጋል።
- የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውን ሕፃናት ለይቶ ከበጎ አድራጎት ክፍል ጋር በመሆን እንዲረዱ ያደርጋል።
- የሕፃናት/የአባላት የመንፈሳዊ ሕይወት ላይ :- ሕፃናት በሃይማኖታቸው ፀንተው የእግዚአብሔርን መንግስት እንዲወርሱ, ለቤተክርስቲያን፣ ለሀገር ፣ለቤተሰቦቻቸው እንዲጠቅሙ በስነ ምግባር የተመሰገኑ እና ሁለገብ የሆኑ ሕፃናትን ለማፍራት ከመደበኛ ትምሀርት ውጭ የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት፣የዝክር እና የአንድነት፣የጉዞ መርሐግብሮችን ያዘጋጃል በልዩ ሁኔታ በሕፃናት የሚከበረው የልደት እና የሆሳዕና በዓል ላይ ነዳያንን በማብላት እና ልብስ በመስጠት እንዲያከብሩ ይደረጋል።ሁሉም አባላት/ሕፃናት የንስሐ አባት እንዲኖራቸው እናም ንስሐ እንዲገቡ በማድረግ በህብረት የሚቆርቡበትን መርሐግብር ያዘጋጃል ።
ወደፊት ለመስራት የታሰበው
- አሁን እየተሰራ ያለው በሙሉ እንዳለ ሆኖ ነገርግን ወደፊት ለማሻሻል እና ለመስራት የታሰበው
- አሁን የተዳከሙ ስራዎችን ማጠናከር የፈጠራ ስራ እና የእደጥበብ ትምህርቶች እንዲጀመሩ ማድረግ
- አማርኛ ቋንቋ ለማይችሉ ሕፃናት መንፈሳዊ ትምህርት በኦሮምኛ እንዲማሩ መርሐግብር ማዘጋጀት
- ወላጆች በወር አንድ ጊዜ መንፈሳዊ ትምህርት እንዲማሩ እና እንደ አስፈላጊነቱ የተለየዩ ስልጠናዎችን እንዲወስዱ ማድረግ
- በህብረት የሚቆርቡበትን መርሐግብር ለሕፃናት ብቻ ሳይሆን ለክፍሉ አባላት፣ለሚያስተምህሩ መምህራን እና ለወላጆች ጭምር ማዘጋጀት
- አሁን እየተሰራ ያለዉን የተማሪዎችን ዳታ(data) ወደ ዳታ ቤዝ መቀየር እና ለተማሪዎች መለያ ቁጥር መስጠት እና መቆጣጠሪያ (አቴንዳንስ) ወደ ዲጂታል መቀየር