Felegetibeb Sunday school EOTC

ፅህፈት ቤት

  •  የሰ/ት/ቤቱን ጠቅላላ ጉባኤና የሥራ አስፈፃሚ ጉባኤውን ሰብሰባዎችን በሰብሳቢነት ይመራል፣
  • የጠቅላላ ጉባኤና የሥራ አስፈፃሚ ጉባኤውን ውሳኔዎችን በፊርማው ለሚመለከታቸው ሁሉ ያስተላልፋል፣ አፈጻጸማቸውንም ይከተላል፡፡
  • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሥራ አስፈፃሚ ጉባኤውን ለአስቸኳይ ስብሰባ ይጠራል፡፡
  • ከሰ/ት/ቤት ጽ/ቤት የሚወጡ ደብደቤዎች በፊርማው ያፀድቃል፡፡

የሰ/ት/ቤት ምክትል ሰብሳቢ ተግባርና ላፊነት

  • የሰ/ት/ቤት ሰብሳቢ በማይኖር ጊዜ ተክቶ ይሰራል
  • ሰብሳቢውን በሚያስፈልገው ሁሉ ያግዛል
  • በሰ/ት/ቤት ደረጃ የሚዋቀሩትን ኮሚቴዎችን ከሰብሳቢው ጋር በመሆን ይመራል

የሰ/ት/ቤት ፀሐፊ

  • የሰ/ት/ቤቱን ጠቅላላ ጉባኤና የሥራ አስፈፃሚ ጉባኤ የሚወያይባቸውን አርዕስት ነገር /አጀንጃዎችን/ ከሰብሳቢው ጋር በመመካከር ያዘጋጃል
  • ጉባኤያቱ ተነጋግረውበት ያሳለፉትን ውሳኔ በቃለ ጉባኤ አዘጋጅቶ በማስፈረም ለሚመለከተው ያስተላልፋል
  • የጠቅላላ ጉባኤውንና የሥራ አስፈፃሚ ጉባኤውን ልዩ ልዩ መዛግብቶችና ሰነዶችን በጥንቃቄ  ይይዛል

ኢንጂነር አበበ ደምሴ
የፈለገ ጥበብ ሰ/ት/ቤት ሰብሳቢ (2015 -2017)