በፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት የመንፈሳዊ ዜማ መሳሪያ ተቋም የ8ኛ ዙር የመንፈሳዊ የዜማ መሳሪያ አስመረቀ
በደብረዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት የፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ልማት ተቋም ስር የሚገኘው የፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት የመንፈሳዊ ዜማ መሳሪያ ተቋም የ8ኛ ዙር ያስተማራቸውን የበገና፤መሰንቆ፤ክራር ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 29/2017 ዓ.ም በሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና ስራ አመራር ኮሚቴዎች፤ወላጆች፤ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ያስመረቀ ሲሆን የ9 ኛ ዙር መደበኛ እና የ4ኛ ዙር የ3 ወር የክረምት ስልጠና የጀመረ መሆኑን በታላቅ ደስታ እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ከታች ባለው ስልክ ላይ በመደወል ያናግሩን።
+251961087411
+251924102840
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጀሰ መምሪያ ማኀበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል የቢሾፍቱ አደአ ፅህፈት ቤት 55ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አከናወነ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጀሰ መምሪያ ማኀበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል የቢሾፍቱ አደአ ፅህፈት ቤት የ 2017 ዓ.ም 55ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በ29/2017 ዓ.ም ያከናወነ ሲሆን የመርሀግብር መክፈቻ ፀሎት ከተደረገ በኃላ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በወረዳ መዕከሉ ሰብሳቢ የተደረገ ሲሆን ከዚያ በመቀጠልም በደብረዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት ፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን ምድብ ወረብ የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም የትምህርት መርሀግብር ተጀናውንዋል።
በዕለቱም የፅህፈት ቤቱ ሪፓርት እና ከአጋር አካላት ጋር የሚሰሩ እቅዶች በቀሲስ ሀረገወይን የቀረበ ሲሆን ከዚያ በመቀጠልም ኦዲት ሪፓርት እና እቅድ ከርብዋል። ከእነዚህ መርሀግበሮች በመቀጠልም ማህበሩ ወዳዘጋጀው የምሳ ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን ከምሳ መርሀግብር በመቀጠልም ከታዳሚ አካላት የተኑስትን ጥያቄዎች በስራ አስፈፃሚዎች ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በመጨረሻም የ2018 ዓ.ም እቅድ እና የስራ አስፈፃሚ ምርጫ በአስመራጭ ኮሚቴ በበላይነት የተመረጠ ሲሆን በአዳማ ማዕከል ተወካይ አባቶች መልዕክት እና ፀሎት ዝግጅቱ ተጠናቋል።
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ “መጽሔት ዘተዋሕዶ” የተባለ የጥናትና ምርምር መጽሔት ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ አደረገ።
ሪፖርተር መ/ር ጌታቸው በቀለ
(#EOTCTV ሰኔ ፲፰ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም)
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መጽሔት ዘተዋሕዶ (Journal Of Tawahedo) የተባለውን የጥናትና ምርምር መጽሔት በሰማንያ ዓመቱ አዘጋጅቶ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት፣ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የመገናኛ ብዙኃን ድርጅት የበላይ ኃላፊና የምሥራቅ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት አስመርቋል። ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ መጽሔት ዘተዋሕዶን ይፋ አድርገዋል።
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በተመሠረተ በሰማንያ ዓመቱ ያዘጋጀው መጽሔት በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ሰባት ጽሑፎችን ይዟል። አምስቱ ጥናታዊ ጽሑፎች ሲሆኑ፣ ሁለቱ የመጻሕፍት ዳሰሳ ናቸው። ከአምስቱ ጽሑፎች ውስጥ ሦስቱ በእንግሊዝኛ፣ ሁለቱን በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ ናቸው።
የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አብርሃም አዱኛ እንደተናገሩት ጥናትና ምርምር ማዕከሉ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ሥራዎችን የሠራ መሆኑን ገልጸው ዛሬ መጽሔት ዘተዋሕዶን ይፋ የምናደርግበት ነው፣ ዩኒቨርሲቲው በተመሠረተ በሰማንያ ዓመቱ የጥናት መጽሔቱን ማሳተሙን ገልጸዋል።
ፕሮፌሰር አባ ኃይለ ገብርኤል ግርማ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ እያለ በ፩፱፻፺፱ ዓም Journal of Holy Trinity የተባለ የጥናት መጽሔት አሳትሟል፣ አሁን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የሆኑት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በወቅቱ በነበረው የምንኩስና ስማቸው፣፣፣ የሥነ ምግባር ምንነት በመጽሐፍ ቅዱስ በሚል ጥናታዊ ጽሑፍ አስነብበውን ነበር ፣ በዚህ እትምም The Role of Servant Leadership In The Ethiopian Orthodox Tawahedo Church፡ A Literature Review በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል በማለት ታሪካዊ ትስስሩን አብራርተዋል።
መጽሔት ዘተዋሕዶ ላይ ወደፊት የቤተክርስቲያን፣ የማኅበረሰቡን ችግር ፈቺ የሆኑ የምሁራን ጥናታዊ ጽሑፎች የሚወጡበት፣ በሀገር ቤትም በውጭም ያሉ የሚሳተፉበት እንደሚሆን አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ መጽሔት ዘተዋሕዶ ይፋ መሆኑን ገልጸው ዩኒቨርሲቲው የትናንት መሠረቱን ሳይለቅ፣ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተካክሎ፣ ተወዳድሮ ለሚቀጥለው ዓመት ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጃል፣ ወደፊትም ሌሎች ጉዳዮችንም በማካተት ዩኒቨርሲቲውን የሚያሳድግ ሥራ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የቀደሙት አባቶች ብራና ዳምጠው፣ ቀለም በጥብጠው ጽፈዋል። ዛሬም የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ዕውቀትን ለበርካታ ዘመናት ሲያከፋፍል ቅይቷል፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሌሉበት ዓለም የለም ያሉት ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ አያይዘውም ከላይ እስከ ታች ተናባችሁ፣ በፍቅር ሆናችሁ ሠርታችኋል። ያዘጋጃችሁት መጽሔት በውስጡ ጥበብ፣ ዕውቀት አለው። ይህን የሚያነብ ሁሉ ዕውቀት እያካፈላችሁ ነው። በታላላቅ ሊቃውንት፣ ታላላቅ ደቀመዛሙርት ይገኛሉ። በፍቅር፣ በመተማመን ይህን ዩኒቨርሲቲ ከዚህ የበለጠ እንድታሳድጉት እግዚአብሔር ያበርታችሁ ብለዋል።
በምረቃው መርሐ ግብር ላይ የዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች፣ መምህራን፣ ተማሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ከተመሠረተ ፲፱፻፴፯ ዓም ጀምሮ በሰማንያ ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ ስታንዳርድ የጠበቀ ትምህርታዊ መጽሔት(Acadamic Journal) ማሳተሙ ይታወቃል።