Felegetibeb Sunday school EOTC

የሥራ አስፈጻሚ/አመራር ጉባኤ

የሰ/ት/ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤው ሆኖ የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራትና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡

  • በጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔና በሰ/ት/ቤቱ ደንብ መሠረት የሰ/ት/ቤቱን አጠቃላይ አገልግሎትና መንፈሳዊ እንቅስቃሴ በበላይነት ይመራል፡፡ያስተባብራል፡፡
  • የሰ/ት/ቤቱን ጠቅላላ ጉባኤ ለስብሰባ ይጠራል፡፡
  • የቁጥጥር ክፍልና የልማት ተቋማት አስተዳደር ኃላፊዎችን ዕጩዎች መርጦ ለጠቅላላ ጉባኤው በማቅረብ ያጸድቃል፡፡ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ከሰ/ት/ቤቱ ዓላማና ደንብ አኳያ በተገቢው መንገድ መወጣታቸውን ይገመግማል፣ ይቆጣጠራል፡፡
  • በሥራና በአገልግሎት ሂደት ለሚከሰቱ ችግሮች ከሰ/መ/ጉባኤና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሔ ይፈልጋል፡፡
  • የሰ/ት/ቤቱን የወደፊት ዕቅድና በጀት ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ እንዲጸድቅ ያደርጋል፣የጸደቀውንም ዕቅድና በጀት በየዓመቱ እየከፋፈለ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
  • ስለሰ/ት/ቤቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴና አገልግሎት የወጣውን ዕቅድና አፈጻጸም በየስድስት ወሩ አንድ ጊዜ ለሰ/መ/ጉባኤና ጠቅላላ ጉባኤው በጽሑፍ ሪፖርት ያደርጋል።
  • በዕቅድ ዝግጅቱም ሆነ በአፈጻጸም ሪፖርቱ ላይ ከጠቅላላ ጉባኤውና ከሰ/መ/ጉባኤ የሚሰጠውን አስተያየትና መመሪያ በመቀበል ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
  • ሰ/ት/ቤቱ በሚያደርገው ልዩ ልዩ አበይት መርሐግብሮችን ለሰ/መ/ጉባኤ ለሰ/መ/ጉባኤ በማሳወቅ ከሰ/መ/ጉባኤ ተወካይ እንዲገኝ ያደርጋል፡፡
  • በማናቸውም ሰ/ት/ቤቱን በሚመለከቱ ጉዳዮች ከሰ/መ/ጉባኤ ጋር በቅርብ በመገናኘትና በመመካከር ይሰራል፡፡