Felegetibeb Sunday school EOTC

የልማት ተቋማት አስተዳደር ክፍል

አስተዳደሩ ንዋያተ ቅዱሳትና ስጦታ ዕቃዎች ማምረቻ፣ የሥርጭት እና ማከፋፈያዎች ማስተባበሪያ፣ ንብረት ቆጠራና ምዝገባና የምግብና ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚባሉ አራት ን/ክፍሎች አሉት፡፡ አስተዳደሩ ተጠሪነቱ ለስራ አመራር ጉባኤ ሆኖ የሚመራው ግን በስራ አመራር ጉባኤ በሚሰየመው ቦርድ/ኮሚቴ ሲሆን የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡

  • የሰ/ት/ቤቱን የአገልግሎት አቅም ለማጎልበት ገቢ የሚያስገኙ የልማት ሥራዎችን (ምግብ ቤት፣ ት/ቤት፣ ዳቦ ቤት፣ ሱቅ፣ ንዋየ ቅዱሳት ማምረቻ…..) አጥንቶ ይተገብራል
  • የቤተክርስቲያንን ሥርዓት የጠበቁ ጋዜጦችን፣ መጽሔቶችን፣መጽሐፍትን፣ድምጽ እና የድምጽ ወምስል ውጤቶችን፣ንዋየ ቅድሳትን፣መብዓዎችን እንዲሁም የስጦታ ዕቃዎችን ያመርታል ያከፋፍላል
  • በሰ/ት/ቤቱ ስር፣ ስም እና ከሰ/ት/ቤቱ ጋር በተያያዘ ለሚከፈቱ የልማት ተቋማት መመሪያ ያወጣል ያንቀሳቅሳል፡፡
  • ልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎችን ማለትም የጽፈት መሳሪያ መሸጫ፣ ፎቶ ኮፒ፣ የመጠረዝና ወዘተ ስራዎችን ይሰራል