Felegetibeb Sunday school EOTC

የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል

የክፍሉ አላማ

 

  • የቤተክርስቲያንን ልዕልናን በዓለም ላይ እንዲታይ ማስቻል
  • የእርስ በእርስ ግንኙነቶች ማጠንከር
  • በቤተክርስትያን ላይ የሚነሱ ማንኛውም ችግሮች መፍትሔ ሀሳብ ማምጣት
  • የቤተክርስትያን ልጆች በኢኮኖሚ ማሳደግ
  • ሰንበት ትምህርትቤቱ የተሻለ የአስራር ሂደት እና የመረጃ አያያዝ ስልትን እንዲኖር ያደርጋል

የክፍሉ ተግባር እና ሀላፊነት

ተጠሪነቱ ለሰ/ት/ቤቱ ጽ/ቤት ሆኖ የሰ/ት/ቤቱን የመረጃ ፤ ሚዲያ እና ሕዝብ ግንኙነት ሥራዎች በበላይነት የመምራትና የማስተባበር ሓላፊነት ያለው ሆኖ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዋና ዋና ተግባሮች እንዲሁም በውስጥ መመሪያ በዝርዝር የሚሰጡትን አገልግሎቶች የሚያከናውን ይሆናል፡፡

  • በሰ/ት/ቤቱ የሚከናወኑ የብሮድካስት መርሐ-ግብሮችን፣ የኅትመትና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ሥራዎችንበሙሉ ያስተባብራል፤ ይመራል፡፡
  •  ከትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንንእምነት ታሪክ ትውፊት ዶግማና ቀኖና የጠበቁ ትምህርትና የኅትመት ውጤቶችን በልዩ ልዩ ቋንቋዎችበማዘጋጀት እና/ወይም በመተርጎም ብሮድካስት መርሑግብርን ጨምሮ የኅትመትና የኤሌክትሮኒክስሚዲያ ውጤቶችን በማዘጋጀት ያሰራጫል።
  • ከእገልግሎት ክፍሎች ጋር በመተባበር የብሮድካስት መርሐ-ግብርን ጨምሮ የኅትመትና የኤሌክትሮኒክስሚዲያ ውጤቶችን በማዘጋጅት ያሰራጫል፤ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ- ግብሮችንና የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት የጥናቱን ውጤት የማስረጽ ሥራዎችን ያከናውናል፡፡
  • የሰ/ት/ቤቱን የማኅበራዊ ሚዲያዎች እና ሌሎችን ማንኛውንም ሚዲያ ይቆጣጠራል፤ይመራል፤
  • የሰ/ት/ቤቱን የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን ይሠራል፤
  • በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎች እንዲጠናከሩ ያግዛል ሕገ ቤተክርስቲያንን ጠብቆ በየደረጃው ካሉት የቤተ ክርስቲያን አካላት የሚሰጡትንና በሥራ አስፈጻሚ ተቀባይነት አግኝተው የሚሰጡትን ተጨማሪ አገልግሎቶች ይፈጽማል፡፡
  • ሰ/ት/ቤቱ ዘመናዊ የመረጃ ቋት እንዲኖረውና መረጃዎቹ በመረጃ ቋቱ እንዲጠበቁ ያደርጋል
  • የሰት/ቤትን የፕሮሞሽንና የቅስቀሳ ሥራዎች ይሠራል፡፡
  • በማንኛውም የስትራት፣ የአባላትና ወላጆች መንፈሳዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ጥናትያደርጋል፣ የፕሮዳክሽን ስራዎችን ይሰራል፣ በሰ/ት/ቤቱ ሚዲያ ያሰራጫል
  • ከቤተ ክርስቲያን፣ ከመንግስትና የግል ሚዲያዎች ጋር የቤተ ክርስቲያንን ሕግ ጠብቆ ቦትብብርይሰራል
  • የሚዲያው ቋንቋ ግዕዝ፣ አማርኛና አፋን ኦሮሞ ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሌሎችን ቋንቋዎችንመጠቀም ይችላል
  • የሚዲያ አርማ፣ የስርጭት ጊዜ፣ በጀት፣ እና አምዶች በስራ አመራሩ እየፀደቁ አገልግሎት ላይ ይውላል
  • ሰ/ት/ቤትን የማስተዋወቅ፣ ሰ/ት/ቤትና ቤተክርስቲያንን የመጠበቅ ስራዎች ይሰራል
  • በፈለገ ጥበብ ሰ/ት/ቤት ስም የተከፈተውን የፈለገ ጥበብ ሚዲያ፣ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ጦር እናሌሎች አውታሮችን በኃላፊነት ያስተዳደል ይመራል ይቆጣጠራል

መልዕክት ከክፍሉ

  • የፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት የመረጃ ሚዲያ እናህዝብ ግንኙነት ክፍል ሰኔ 2014 ዓ.ም ተጠሪነቱ ለሰ/ት/ቤቱ ጽ/ቤት ሆኖ የሰ/ት/ቤቱን የመረጃ ፤ ሚዲያ እና የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎች በበላይነት የመምራትና የማስተባበር ሓላፊነት ያለው ኖሮት ተመሰረተ።
  • ክፍሉምንም በሀላፊነት በመቀበል የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል በውስጡ የክፍሉን ተክባር እና ሀላፊነቶችን የሚፈፅሙለትን ተያያዥ የሆኑ 5 ንዑሳን ክፍሎችን ማለትም የመረጃ ንዑስ ክፍል ፣ ሚዲያ ንዑስ ክፍል ፣ህዝብ ግንኙነት ንዑስ ክፍል ፣ ፋይናንስ እና ንብረት ንዑስ ክፍል በማድረግ በማደራጀት እና ለእያንዳንዱ ንዑሳንክፍላት ተግባር እና ሀላፊነት በማስቀመጥ እና የንዑስ ንዑስ ክፍላትን በማደራጀት ስራውን መረ።
  • በመሆኑም ክፍሉ አዲስ በመሆኑማ ከዚህ ቀደም ሰንበት ትምህርት ቤቱ ቀደም ያሉ ልምዶች ባለኖራቸው ክፍለሰቱን ለማደራጀት በተለያዩ ዘርፎች ስልጠና ከትምህርት እና ስልጠና ክፍል ጋር በመተባበር ለተመረጡ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት በመስጠት የክፍሉን ንዑሳን እናየንዑስ ንዑስ ክፍላትን እንዲይዙ አድርጓል እያደረገም ምገኛል።
  • በተጨማሪም ክፍሉ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ሌሎች ስራዎችን ያከናወነ እና እያከናወነ ያለ ሲሆን ለምሳሌ ያክል በሰንበት ትምህርት ቤቱ ስም የተከፈቱ 15 በላይ የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናሎችን ፤ የፌስብክ ገፃችን ፣ የኢንስታግም ገፆችን እንዲሁም ከ14ሺ በላይ ተከታዮችን ያፈራውን የቲክቶክ እና ከ3700 በላይ ተከታዩች ያሉት የዩቲዩብ ገፅን በሀላፊነት እየተቆጣጠረ ይገኛል።በተጨማሪም ክፍሉን የሚመለከቱ ስራዎችን (ገንዘብ የሚያስገኙ ተግባራት ) በመለየት ማለትት የፎቶ እና ቪዲዮ ቀረፃ ፣ የዲኮር ስራ ፣የሞንታርቦ ስራ እና ሌሎች ተግባራትን በመለየት ፈለገ ጥበብ ፕሮዳክሽን በሚል ስያሜ የሚጠራ አብድ ፕሮዳክሽን በማዋቀር የተለያዩ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ እና ለአባላቱ ገንዘብ የሚያስገኙ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
  • በተጨማሪም የሰንበት ትምህርት ቤቱን ሎጎ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ትርጉም ባለው መልኩ ለታሪይ ይቀመጥ ዘንድ አዘጋጅቶ በፅህፈት ቤት በማስገምገም የማፀደቅ ስራን ሰርትዋል።
  • ክፍሉ ወደፊት ከተሰጠው ተግባርና ሀላፊነ አንፃርብዙ ተግባራት የሚጠበቁበት ሲሆን በሚቀጥሉት ጊዜያት የሰንበት ትምህርት ቤቱን የስራ አሰራር ባህልን በመገምገም ለስራ ያመች ዘንድ የሚሆኑ ሲስተሞችን መዘርጋ ፣ የሰንበት ት/ቤቱን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ሰአት ያለበትን ሁኔታ የሚገልፁ መረጃዎችን በመሰብሰብ ወደመረጃ ቋታቸው እንዲገብ እና እንዲመዘገብ የማድረግ ስራዎችን ፣በሰንበት ት/ቤት ውስጥ የሚነሱ ችግሮችን በማጥናት እና የጥናቱን ውጤት እና መፍትሄ ለሚመለከታቸው አካላት የማስተላለፍ ስራ፣ ክፍሉን በቁሳቁስ እና በሰው ሀይል የማደራጀት ስራዎችን ፣ የሰንበት ት/ቤት ማህበራዎ ግንኙነት እንዲጠነክር የማድረግ ስራዎች ፣ ሰንበት ት/ቤቱ ኢኮኖሚ አሁን ካለው ይበልጥኑ እንዲጨምር አዳዲስ ሀሳቦችን ለፅህፈት ቤት በማቅረብ ስራዎችን የሚያከናው ሲሆን ይሄንን እና ሌሎች ተግባራትን በጋራ እንከውን በማለት የቤተክርስቲያን ልዕልናን እናስጠብ ዘንድ ቅዱስ እግዚአብሔር በቸርነቱ ይዳን እያልን መልዕክታችንን እናስተላልፋለን ።