ጠቅላላ ጉባኤ
የሰ/ትቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠሪነቱ ለደ/ዘ/ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ሰ/መ/ጉባኤ ሆኖ የሚከተሉትን ተግናርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡
- የሰ/ት/ቤቱን አጠቃላይ ጉዳዮችን ይወስናል
- የሰ/ት/ቤቱን አጠቃላይ የሥራ ሂደትና አገልግሎት ይገመግማል
- የሰ/ት/ቤቱን ዕቅድና በጀት ያጸድቃል
- የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላትን ይመርጣል፣ ከሥራ አስፈጻሚ አባላት መካከል የሰ/ትቤቱን ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢና ጸሐፊ ይሰይማል ለሰ/መ/ጉባኤም አቅርቦ ያጸድቃል
- በሥራ አስፈጻሚ ጉባኤው ተመርጠው የሚቀርቡትን የቁጥጥር ክፍል ኃላፊ እና የልማት ተቋማት አስተዳደር ኃላፊን ያጸድቃል
- ጠቅላላ ጉባኤው በዓመት ሁለት ግዜ በሰ/ት/ቤት አዳራሽ ይሰባሰባል
