መዝሙርና ኪነ-ጥበብ ክፍል ክፍሉ የመዝሙር ዝግጅት ን/ክፍል፣ የኪነ-ጥበብ ዝግጅት ን/ክፍልና የስነ-ፅሑፍ ዝግጅትና ግምገማ ን/ክፍል የሚባሉ ሶሰት ን/ክፍላት ሲኖሩት ተጠሪነቱ ለስራ አስፈጻሚ ሆኖ የሚከተሉት ተግባራና ኃላፊነት ኖረዋል፡፡ የሰ/ት/ቤቱ መዝሙር ክፍል በሰው ኃይልና በቁሳቁስ በማጠናከር የመዝሙር መርሐግብሮችን ያዘጋጃልአባላት መዝሙር እንዲያጠኑ፣ በሰ/ት/ቤቱ አባላት በአንድነት መርሐግብር ላይ ያቀርባልስለያሬዳዊ መዝሙሮች /ዜማ/ የሰ/ት/ቤቱ አባላትንና የክፍሉ አባላት ግንዞቤ እዲኖራቸው ጥረት ያደርጋልስነ ጽሑፎችን ያሰባስባል፣ ያስገመግማል በልዩ ልዩ መርሐግብር ላይ እዲቀርቡ ያደርጋልመንፈሳዊ ጽሑፎችን ዶክመንት አድርጐ ያስቀምጣል እዲሁም የሥነ-ጽሑፍ ውድድር አዘጋጅቶ ለሚያሸንፉት ይሸልማልመንፈሳዊ ትርዒቶችን /ድራማዎት፣ ጭውውት እንዲደርሱ ተገምግመው ለምዕመናን / ለአባላት / እንዲታዩ ያደርጋል እንዲሁም የድራማ ድርሰቶችን ዶክመንት ያደርጋል